Tuesday, 31 May 2016
ኢትዮጵያውያን ይህን ፅሁፍ ታግሳችሁ እንድታነቡት እፈልጋለሁ፤ የክሮስ ቸርች አባላት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው 50000 ቸርች በኢትዮጵያ ሊገነቡ ፈቃድ አግኝተዋል፤ ለምን? - by Daniel Tomas
ውድ ኢትዮጵያውያን ይህን ፅሁፍ ታግሳችሁ እንድታነቡት እፈልጋለሁ፡፡
1ኛ፣ሰሞኑን የክሮስ ቸርች አባላት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሃምሳ ሺ ቸርች በኢትዮጵያ ሊገነቡ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
2ኛ፣የ666 የማይክሮ ችፕ ገጠማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገሮች ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡
3ኛ፣የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አይነትነት አሰራር የኢትዮጵያ ዜጎች እንዳያውቁና ስለዚህ ጉዳይ እንዳይወሩ የሚያግድ ህግ አርቅቆ ሊያፀድቅ ነው፡፡በእነዚህ ሶስት ነጥቦች ዙሪያ መነጋገር አለብን፡፡
በቅርቡ የሰማችሁት ዜና እንዳለ እርግጠኛ ነኝ፡፡ክሮስ ቸርች ግሎባል ሚሽን የተባለ እምነት ድርጅት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ 50 ሺ ሃምሳ ሺ ቤተክርስቲያን ሊያቋቁም ነው፡፡ስራውን በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎች ክልሎች በይፋ ሊጀምር ነው፡፡እነዚህ ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከአገራችን ባለስልጣናት ጋር ተወያተዋል፡፡ፕሬዘዳንታችን ጨምሮ ሁሉንም አግኝተው ተነጋግረው አስፈቅደውና ተፈቅዶላቸው ነው ስራቸውን የጀመሩት፡፡ሁኔታው እንግዳ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም ነው፡፡ዓላማቸው ወንጌልን መስበክ እንደሆነና በኢትዮጵያ ከፍተኛ በጀት መድበው 50 ሺ ቤተክርስቲያን መትከል ነው፡፡እንግዲህ ይህን ጉዳይ በሚመለከት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ለየራሳችን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ይኖራል፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ሰዎች የሚያስፈቅዱት መንግስትን ወይስ የሚመስላቸውን ምዕመን?ማለት ስለወንጌል ሰበካ ነው አይደለም የሚለውን መንግስት ነው የሚያጣራው?ወይስ የመፅሐፍ ቅዱስ አማኞች?እንደ ሐይማኖተኛ ሳይሆን እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ቃል ለነሱ ጥያቄ ማቅረብ ያለበት ማነው?ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ ‹‹በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሐሰተኛ /ሃሳዊ/ሰዎች ይነሳሉ ብዙ ታዓምራትንም ያደርጋሉ ህዝቡንም ያስታሉ ስለዚህ መርምሩ›› ይላል፡፡ይህን የመመርመርና መንፈስን የመለየት ተግባር የማን ነው?ኢትዮጵያ ውስጥ ማንን ነው የሚመለከተው?የኔ ጥያቄ ነው፡፡
ምንም ይሁን በብዛቱ አስደንጋጭ መሆን ብቻ በርካታ ጥያቄዎችን እንድናነሳ እንገደዳለን፡፡
ልብ በሉ 50 ሺ ቤተክርስቲያን እንዲሁ በአይምሮዋችሁ፤ጎንደር 44 ታቦት፣ጎጃም 44 ታቦት፣ወሎ 44 ታቦት አዲስ አበባ ይህን ያህል፣ ጂማ ይህን ያህል፣እያላችሁ ቁጥሩን ለመገመት ሞክሩ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ቦሌ አንድ መካነ ኢየሱስ፣ጦር ሃይሎች አንድ፣ ኮተቤ፣ ሸጎሌ፣ እያላችሁ ለመቁጠር ሞክሩ፡፡በተመሳሳይም የሌላውን ኢትዮጵያዊ ሐይማኖት የማምለኪያ ስፍራ ቁጠሩ፡፡ወይም ለመገመት ሞክሩ፡፡
ከዚህ በፊት በአገራችን የነበሩት እነዚያ ሁሉ የማምለኪያ ስፍራ በረጅም ዘመናት ሂደት እየተገነቡና እየተስፋፉ የመጡ ናቸው፡፡በአንድ ጊዜ 50 ሺ የማምለኪያ ስፍራ በኢትዮጵያ የገነባ የእምነት ድርጅት ወይም ተቋም የለም!!
50 ሺን በብር ደረጃ ብትስሉት ወይም ብትገምቱት አምስት እስር ብቻ ናት፡፡በምንም ብትስሉት ቁጥሩ ብዙ ላይመስል ይችላል፡፡በቸርች ወይም በማምለኪያ ስፍራ ደረጃ ሲሆን ግን ምን እንደሚፈጠር አስቡት፡፡
ቦታን በካሬ እየሸነሸናችሁ በደንብ አብሰልስሉት፡፡ለማመን እንቸገራለን፡፡ይህን ያህል ቸርች በመገንባቱ ደስ የሚለው ሊኖር እንደሚችል ሁሉ የሚከፋም ይኖራል፡፡ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ነገር ግን ደስ የተሰኘው አካል እሱ ልክ ነው ብሎ ከያዘው እምነት ጋር እነዚህ ይዘውት የመጡት አይቃረንም ወይ?የሚለውን ማሰብ ለምዕመኑ የሚተው ይሁን በሚል ብንተተወው እንኳን፤ የአካሄዱ አስደንጋጭነት ብቻውን ወደ ሌላ ጥርጣሬ ያመራናል፡፡ጥርጣሬ ብቻ አይደለም ወደ ሌላ ዕውነት ያመራናል፡፡
በእርግጥ ለኢትዮጵያ 50 ሺ ቸርች ያስፈልጋታል?አያስፈልጋትም! ብሎ የሚወስነው አካል ማነው?እስከዛሬስ የት ነበሩ?50 ሺ ቸርች የሚያስፈልገው ምዕመን ስለመኖሩስ እርግጠኞች ናቸው?ወይስ ምዕመኑ በዝቶ ስለተጥለቀለቀና ቸርቾች ስለጠበቡ?የነዚህ ሰዎች ትክክለኛ ኣላማ ምንድነው?ዓላማቸውንስ ለኛ ነግረውናል?ኦኬ መንግስት ማለት ህዝብ ስለሆነ መንግስት ካመነበት በቂ ነው ልትሉ ትችላላችሁ ነገር ግን መንግስት የሰዎችን የነብስ አዳኝ መርጦ ሊሰጥ አይችልም፡፡በዚህ ዙሪያ ያለውን ነገር ለሌላ ጊዜ እናቆየውና ስለተፈቀደላቸው ወይም ስለተሸጠላቸው ቦታ ብቻ እናስብ፡፡ ሃምሳ ሺ ቤተክርስቲን!መቸም ፈረንጅ ሳያቅድና ሳይዘጋጅ እንዲህ አይነት ነገር ይፋ አያደርግም፤ወደ ተግባርም አይገባም፡፡ሲመጡ ደግሞ እኛ ሰይጣን ነን አይሉም፡፡ በቂ ዝግጅት አድርገው ቅዱሳን እንደሆኑ አድርገን እንድቆጥራቸው የሚያደርግ ተግባር እየፈፀሙ ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡
ብቻ ተዘጋጅተው የመጡ መሆናቸው ለማንም ግልፅ ነው፡፡ተመልከቱ፤ለአንድ መኖሪያ ቤት እንኳን 500 ካሬ ሜትር ነው በተለምዶ የምናውቀው፡፡ለቸርች ሲሆን ስንት ይሆናል?አንድ ቸርች በስንት ካሬ መሬት ላይ ያርፋል?ይህ ብቻውን ቀና ነገር ይዘው እንዳልመጡ ያረጋግጥልናል!
50 ሺ ቸርች ሊሰሩ ነው፡፡እያንዳንዱ ቸርች በጣም በጣባቡ 1ሺ ካሬ ቢይዝ ብለን እናስብ፡፡ከዚያ በላይ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ግን ነገሩን እናቅልለው ብለን በ 1ሺ ካሬ አረፈ እንበል፡፡እንዲሁ ጠባባብ ቸርች፡፡50000 ሲባዛ በ 1000 50000000/ሃምሳ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ይሆናል፡፡በ2ሺ ካሬ ካረፈ 100 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ይሆናል፡፡ወደ ሄክታር ቀይሩት!የሚዘገንን ነው!ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላ ነገር እንድታስቡ ልጋብዛችሁ፡፡አንድ ቸርች በአማካይ በጣም በትንሹ ስንት ሰው ይይዛል?ወይም ስንት አባል ይኖረዋል?ቸርች ሲባል አገልጋይ አስተዳዳሪ ሰባኪ ወዘተ…ብዙ ሰው ይኖራል፡፡ምዕመንም ይኖራል፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ቸርች በጣም በትንሹ 1ሺ ሰው ቢይዝ/እስከ 5ሺ እስከ 10 ሺም ሊደርስ ይችላል/በትንሹ አንድ ቸርች 1ሺ ሰው ቢኖረው ብለን ካሰብን 1ሺን በ 50 ሺ ብናበዛው 50000000/ሃምሳ ሚሊዮን ሰው ይኖረዋል፡፡አንድ ቸርች በትንሹ 2ሺ አባል ቢይዝ የ 50 ሺ ቸርች አባላት ብዛት 100000000 /መቶ ሚሊዮን/ ሆነ ማለት ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ በ2015 99 ሚሊዮን ነው፡፡ጠቀለሉት ማለት አይደል?ይህንን ነው አቡነ ፍራንሲስ አንድ ዓለም አንድ ሐይማኖት እያሉ በየአገሩ እዞሩ የሚያሳምኑት!መቸም አንድ ቸርች ከ አምስት መቶ ያነሰ ሰው ይዞ ቸርች አይሆንም፡፡ስለዚህ ጉዳዩ የአንድ ሐይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የኢትዮጵያ እንደሆነ ማሰብ አለብን!ይህን እየሰማንና እያየን ምን እየተከናወነ እንዳለ ማሰብ ካልቻልን ሙሉ በሙሉ ክፉ መንፈስ አይምሮዋችን ተቆጣጥሮታል ማለት ነው! 50ሺ ቸርች!!!
መፅሐፍ ቅዱስ ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ›› ይላል፡፡ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ወይም ይህ ድርጅት መጀመሪያ ቸርቹን ከዚያ ስብከቱን እያሉ ነው፡፡ሙሉውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀስ በቀስ በቁጥጥር ስር እንደሚያውሉትና ሌላ የሐይማኖት ተቋማት እንደሚጠፉ እርግጠኞች ናቸው ማለት ነው፡፡ወንጌል ተሰብኮ ምዕመን እየበዛ ሲሄድ ነው ቸርች የሚስፋፋው፡፡ያውም በራሱ በምዕመኑና በሐይማኖቱ ተከታይ በሚዋጣ ገንዘብ! እንደዚህ ዘሎ እንደ መንገድ ስራ ፕላን 50 ሺ ቸርች የሚባልበት የሐይማኖት ስርዓት የለም፡፡መንግስትስ መሬት መሸጥ ነው የያዘው ወይስ የሀይማኖት ነፃነትን ለማንሰራፋት? እኔ ኦርቶዶክስ ብሆንና አንድ የውጭ የሐይማኖት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ 50 ሺ ቸርች ልሰራ ነው!ቢለኝ ‹‹ኧረ አባ 50 ሺ ቤተክርስትያን በዚች ጠባብ አገር?››ብየ እሞግታለሁ፡፡እኔ ፕሮቴስታንት ብሆን ‹‹50 ሺ የፕሮቴስታንት ቸርች ልናቋቁም መጣን!›› ቢሉኝ፤‹‹ኧረ ፓስተር 50 ሺ ቸርች?››ብየ መቃወሜ አይቀርም፡፡እኔ ካቶሊክ ብሆንና የሌላ አገር ቅርንጫፍ ተቁዋም መጥቶ ‹‹50 ሺ ቸርች በኢትዮጵያ!››ሲለኝ ብሰማ፤‹‹እንዴት?››ብየ መቃወሜ አይቀርም፡፡እኔ ሐይማኖት አልባ ብሆንና ይህን ነገር ብሰማና ባይ፤ ‹‹እንዴ እንዴት?ያገሬ ገበሬ ምን መሬት አርሶ ሊበላ ነው?››ማለቴ አይቀርም፡፡እኔ ከየትኛውም ወገን ብሆን ይህን ዜና መቃወሜ አይቀርም፡፡መንግስትም ብሆን ‹‹ከፍተኛ የሆነ የመሬት ወረራ›› እለዋለሁ፡፡ስለሚፈናቀለው ሰው አስባለሁ፡፡ይህን ያስቀደምኩት ጉዳዩ የሐይማኖትና የሐይማኖተኞች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአገር ህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጭምር ለማስገንዘብ ነው፡፡ይህ ጉዳይ በቀጥታ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሌላው ዓለም ህዝብ በፊት የአውሬው ምልክት የሚባለውን የ666ን ወይም የማይክሮ ችፕ ገጠማን ለማከናወን የተጀመረ ጅምር ወይም የመሰረት ድንጋይ እንደሆነ ከመጠርጠርና ከማሰብ ውጭ ሌላ ስያሜ ልንሰጠው አንችልም!ሌላ ማሰብና መገመት የምንችለው ነገር የለም፡፡ይህን አርማ ደግሞ በቀላሉና በቶሎ አይቀበሉም ተብለው የተፈሩት የኢትዮጵያዊ ዜጎች ናቸው፡፡ በዚህ ሀሳብ የሚስቅ ሰው ካለ ቀስ እያለ እንደሚያለቅስ የታወቀ ነው፡፡‹‹ኢትዮጵያን ይፈልጉዋታል፡፡ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ዘመን ጋር በተያያዘ ትልቅና ወሳኝ የሆነ መንፈሳዊ ነገር በውስጡዋ አለ፤ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ልዩ አገር ናት››ሲባል የሚያፌዙ ምሁራን እንዳሉን እናውቃለን፡፡ግድ የለም ሁሉም በዘመኑ ይፋ ይሆናል!ለታወሩት ሳይሆን ላልታወሩት ነው ነገሩ ግልፅ የሚሆነው፡፡
ይህን ጉዳይ በስተኋላ የምንመለስበት ይሁንና ስለተያያዡ ነገር እንይ፡፡
መፅሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 13 ቁጥር17-18 እንዲሁም ምዕራፍ 14 ቁ 9 ላይ ‹‹የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቁጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል፡፡ጥበብ በዚህ አለ፡፡አእምሮ ያለው የአውሬውን ቁጥር ይቁጠረው፤ቁጥሩ የሰው ቁጥር ነውና፤ቁጥሩም ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ነው፡፡…..ለአውሬውና ለምስሉም የሚሰግድ፤በግንባሩ ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፤….የስሙንም ምልክት የሚቀበል ሁሉ ቀንና ሌሊት እረፍት የላቸውም፡፡››ይላል፡፡ሙሉውን እንድታነቡት እመክራለሁ፡፡
ባሁኑ ሰዓት በአሜሪካና በሌሎች የ666 ማይከክሮ ችፕ /የአውሬው ምልክት ተዘጋጅቶ አልቆዋል፡፡ምስሉን ዝቅ ብላችሁ እንደምታዩት ሂደቱ እየተጠናቀቀ ነው፡፡ይህ ለዓለም ህዝብ ሁሉ የተዘጋጀና በእጅና በግንባር የሚሰጥ ምልክት ተመርቶ ወይም ተዘጋጅቶ ወደ ቀጣዩ ስራ እየተገባ ነው፡፡
የቀረው የስርጭት ጉዳይና ከማን ይጀመር የሚለው ነው፡፡ልብ በሉ፤የግብረሰዶማውያን ህግ ቀድሞ እንዲፀድቅ ተፈልጎ የነበረው በኢትዮጵያ ነው፡፡ሳይሳካ ሲቀር በአሜሪካ ፀደቀ፡፡ከዚያ በዘዴ ተመልሰው መጡ፡፡
በቅርቡ ደግሞ ባራክ ኦባማ ‹‹በሲ ኤን ኤን ቴሌቪዥን ቀርቦ እስከ 2017 ሁሉም አሜሪካዊ ማይክሮችፕን በቀኝ እጁ መግጠም አለበት››የሚል ይፋዊ መግለጫ ሰጠ፡፡የቫቲካኑ ጳጳስም በየአገሩ እየዞረ አሳመነ፡፡
እስካሁን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን ብቻ ተቀብለው ሌላው በማጉረምረም ላይ ይገኛል፡፡ሆኖም የሚቀርለት የለም፡፡ይህ በሆነ ማግስት ልክ እንደ ግብረሰዶሙ ህግ ሌላው ዓለም ቀስ ብሎ መቀበሉ እንደማይቀር ስለሚታመን በዋናነት ትኩረቱ ኢትዮጵያና ህዝቡ ላይ ሆነ፡፡ማይክሮ ችፕን በቀኝ እጁ ያላስገጠመ ሰው መሸጥ መለወጥ አይችልም፡፡በዚህ ማይክሮችፕ አማካኝነት የገንዘብ አካውታችን፣የደም ዝውውራችን፣ያለንበት ቦታ፣በአይምሮዋችን ያለው አስተሳሰብ ሁሉንም ውስጡ ባለው ip numbere አንዱ አካል ይቆጣጠራል፡፡ልጆችን ማስተማር፣ታሞ መታከም፣ገንዘብ መላክ፣ገንዘብ መቀበልም ሆነ ምንም ማድረግ ስለማይቻል ነገሩ የውዴታ ግዴታ የሆነበት ይቀበላል ነው ቀመሩ፡፡ ያልተቀበለ እምነቱን ጠብቆ መሞት ይችላል፡፡ለኢትዮጵያውያን ግን እንደሌላው ዓለም ህዝብ በፍላጎት ሳይሆን በሀይል ለመጫን ነው ፍላጎታቸው፡፡ለዚህም ይረዳ ዘንድ የበግ ለምድ ለብሶ የመጣ ተኩላ እንደሚባለው በወታደራዊና በደህንታችን ላይ ምናምን..በሚል ሽፋን የተሰጠው መርዝ የሆነ ህግ ከ ሶስት ቀን በፊት በኢትዮጵያ ላይ ተረቆ በፓርላማ ሊፀድቅ ነው፡፡ይህ ህግ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ህጉ ከምንም ነገር ጋር እንደማይያያዝ ተደርጎ በይፋ የተገለፀውንና ሪፖርተር ጋዜጣ ያወጣውን ብዙዎቻችሁ አይታችኋል፡፡
እንነጋገርበት!
ይህን ህግ ምን አገናኘው ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ነገር ግን መቶ በመቶ ይገናኛል፡፡ሌሎችን አንቀፆች ስናይም በደንብ ይገባናል፡፡
ይህ ህግ በኢትዮጵያ ፀደቀ ማለት ኢትዮጵያውያን አይናቸውን ጨፍነው ስለምንም ነገር ሳያውቁ ወደማያውቁት ጥልቅ የጭለማ ህይወት ውስጥ እንዲገቡ ማድረግ ማለት ነው፡፡ይህ ህግ በኢትዮጵያ ፀደቀ ማለት የተማረው ጥቂቱ ህዝብ በወሬ ደረጃ እንኩዋን ላልተማረ ወገኑ አንዲት ፍሬ ያላት ሃሳብ ማስተላለፍ አይችልም ማለት ነው፡፡ህጉ ፀደቀ ማለት የኢትዮጵያ ህዝብ በጅምላ ለመስዋዕትነት የሚነዳ በግ ተደረገ ማለት ነው፡፡በግ ሲነዳ ለግጦሽ ይሁን ለእርድ አያውቅም፡፡ይህ ህግ ቀጥተኛ ትርጉዋሜው ዓይናችሁን ጨፍኑና እኛ እናሞኛችሁ፤ጆሮዋችሁን ድፈኑና እኛ እንስማላችሁ ማለት ነው፡፡ህጉ ፀደቀ ማለት ወላጆች ስለ ልጆቻቸው ምንም መብት የላቸውም ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ ስለ ህፃናት ስርቆት አንድ ዓለም አቀፍ መረጃ ቢኖር ያን መረጃ ኢትዮጵያውያን ወላጆች ሰምተው መጠንቀቅ አይችሉም፡፡ዓለም በሂውማን ትራፊክ እየተሰቃየችና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናት ተሰርቀው ለክፉው መንፈስ ለመስዋዕትነት እየዋሉ ነው፡፡ይህን መረጃ ከዓለም የመረጃ መረቦች ወስደን በብቸኛዋ መተማመኛችን ተርጉመን በፌስ ቡክ ብንለቅና ወላጆች ተጠንቀቁ የሚል ነገር ፅፈን ፖስት ብናደርግ፤በህዝቡ ዘንድ ሽብር በመፍጠር በሚል 25 ዓመት ያሳስራል፡፡በዚህ ምክንያት የሚታሰረው አንድ ሰው ሳይሆን፤ላይክ ያደረገ፣ያነበበ፣ሼር ያደረገ፣ኮሜንት የሰጠ፣ሁሉም ይታሰራል ነው፡፡ስንቱን አስሮ ይችላል?ልትሉ ትችላላችሁ፡፡ጥቂት ሰዎችን ካሰሩ ሌላው ፈርቶ ይተዋል፡፡ደግሞም ለእንዲህ አይነቱ ቀና ተግባር ጊዜ መድበው የሚፅፉት ውስን ሰዎች ናቸውና ዋና ዋናውን ማሰር ብቻ በቂ ሆኖ አግኝተውታል፡፡
ይህ ህግ ፀደቀ ማለት ለምሳሌ ስለ ግብረሶዶማውያን አፀያፊነት ተግባር እየፃፈ ተጠንቀቁ ወገኖቸ፣ልጆቻችሁንም በትምህርት ቤት ስለ ግብረሰዶም ጥሩነት የሚያስተምር ኩዋርኩለም ቀርፀው እያስተማሩ ነውና….እባካችሁ ጥብቅ ክትትል አድርጉ ወዘተ…ተብሎ ቢፃፍ፤ መረጃውም በፎቶና በቪዲዮ ቢደገፍ ያን ያደረገ ሰው ይታሰራል ማለት ነው፡፡ሌላውም ፈርቶ መረጃውን ይፋ ከማድረግ ይቆጠባል ማለት ነው፡፡
ለምሳሌ አንድ ታዋቂ የሐይማኖት አባት በይፋ ግብረሰዶማዊ ቢሆንና መሆኑን የሚያረጋግጥ ይፋዊ መረጃዎች ቢኖሩ እንኩዋን ስለዚያ ታዋቂ የሐይማኖት አባት ግብረሰዶማዊ መሆን መናገርና መረጃውን ማሰራጨት፤መረጃውንም ይፋ አድርጎ ቅኑን ምዕመናን ለማስጠንቀቅ ቢታሰብ አይቻልም፡፡ስም ማጥፋት፣ህዝቡን ማወናበድ በሐይማኖት ላይ ሽብር መፍጠር፣አመፅ ማነሳሳት፣ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በመረበሽ በሚል እስር ይጠብቀናል፡፡ስለዚህ የሚያውቁትም ዝም እንዲሉ ህግ ያስገድዳል!የሚያውቁትም ለማያውቁት መንገር ክልክል ነው! ማለት ይሆናል፡፡እጅግ የሚያሳዝንና ሁላችንንም ሊያስቆጣ የሚችል ህግ ነው፡፡በጣም የሚያሳዝነው ይህ ህግ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበረው በኢትዮጵያ ላይ ብቻ መሆኑ ነው፡፡ለምን ኬንያ ላይ ይህ ህግ አልወጣም?ለምን ኡጋንዳ ላይ ለምን ናይጀሪያ ላይ አይወጣም?ለምን ኢትዮጵያ ላይ?
ይህ የኮምፒውተር ህግ በሚል ሽፋን የወጣው ህግ በቀጥታ ከማይክሮችፕ ገጠማ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ምንም ሳይልና ሳመነታ እንዲቀበል ለማስገደድ እንጂ ለሌላ ለምንም አይወጣም፡፡ነገርየው በኮምፒውተር አይፒ ነምበር ሁሉንም ዜጋ ከመሰለል ጋር የተያያዘ ይምሰል እንጂ ከዚያ ያለፈ ነው፡፡ማይክሮችፕ ሲባልም ልክ ኮምፒውተር ላይ እንዳለው አይ ፒ ነምበር ሰዎች ላይ አይፒ ነምበር መግጠም ማለት ስለሆነ ተመሳሳይ ነው፡፡ኮምፒውተር የሚሰለለው በ ኤ ፒ ነምበ ነው፡፡እናም የ666ን ምልክት ስንቀበልና ደማችን ውስጥ ለዘላለም እንዳይወጣ ሆኖ ሲቀበር የሚቀበረብን ነገር ቁጥር ወይም አይ ፒ ነምበር ነውና በዚያ አማካኝነት በአንድ በጥልቁ ወይም በአውሬው አገዛዝ ስር እንሆናለን ነው፡፡ቴክኖሎጂው ረቂቅ ስለሆነም ለብዙዎች በቀላሉ ላይገባ ይችላል፡፡መረጃ በደንብ ከተለዋወጥን ግን ግልፅ ነው፡፡ያንን ነው እንዳናውቅና እንዳናወራበት የተፈለገው፡፡ይህ ደግሞ በሐይማኖት ስም ነው የሚሰጠው፡፡ስለዚህ አሰራሩን የተቃወመ ኢትዮጵያዊ በኮምፒውተር ህግ ወንጀለኛ ይባላል ይታሰራል ለፍርድ ይቀርባል ነው፡፡
ዜጎች የክፉውን መንፈስ አሰራር እንዳያውቁና እንዳያሳውቁ አውቀውም እንዳያጉረመርሙ በሚል ነጥብ ብቻ ነው ይህ ህግ ያስፈለገው፡፡ለመጀመሪያ ጊዜ የተረረቀውና ለመፅደቅ የተዘጋጀው ደግሞ በኢትዮጵያ ነው፡፡
ልብ በሉ ዓለማችን ላይ ብዙ ሽብር ያለባቸው አገሮች አሉ፡፡ብዙ ጦርነት ያለባቸው አገሮች አሉ፡፡ብዙ የኢንተርኔት መረጃ ጠለፋ የሚከናወንባቸው አሉ፡፡ብዙ የደህንነት ስጋት ያለባቸው አገሮች አሉ፡፡በኮፒውተር ሳይንስ ጣራ የደረሱ አገሮች አሉ፡፡ብዙ ተጠቃሚዎች ያሉባቸው አገሮችም አሉ፡፡የእነዚህ አገራት መንግስታት ግን ይህን አይነት ህግ አላስፈለጋቸውም፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር ስንት እንደሆነ ይታወቃል፡፡እ.ኤ.አ በ 2015 የወጣው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር ልንገራችሁ፡፡ኢትዮጵያ 3.7 ሚሊዮን ህዝብ ኢንተርኔት ይጠቀማል፡፡3.7 ሚሊዮን ህዝብ ፌስቡክ ይጠቀማል፡፡እንግዲህ የሌላውን አገር ስናይ ለምሳሌ ኢንተርኔት ተጠቃሚው 10 ሚሊዮን ይሆንና ፌስ ቡክ ተጠቃሚው 2 ሚሊዮን ይሆናል፡፡ይህ ማለት በሌላው አገር ኢንተርኔት ተጠቃሚ የሚባለው ፌስ ቡክ ተጠቃሚው ብቻ አይደለም፡፡ሌሎች ብዙ ማህበራዊ ድረ ገፆች ስላሉ፡፡ኢትዮጵያ ላይ ግን 3.7 ሚሊዮን ህዝብ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ነው፡፡3.7 ሚሊዮኑም ፌስ ቡክ ላይ ብቻ ነው እንደማለት ነው፡፡ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ተጠቃሚ የሚለው ፌስቡክ ተጠቃሚውን ብቻ ነው ማለት ነው፡፡
ታዲያ ይህ ህግ ለምን አስፈለገ?ከብት ባልዋለበት ለምን ኩበት ይለቀማል?መልሱ ቀላል ነው፡፡ለኢትዮጵያ ህዝብ ብቸኛው የመረጃ መረብ ባሁኑ ሰዓት ፌስ ቡክ ብቻ ስለሆነ ነው፡፡እነ ዩቲዩብ እነ ምናምን አሉ፡፡እነሱን ለማየት አቅም ያለው ውስን ነው፡፡ከቁጥርም አይገባም፡፡ቤታችሁ ውስጥ 10 ሰዎች ካሉ በእርግጠኝነት 9ኙ ፌስ ቡክ እንጂ ቲዊተር ወይም ሌላ አይጠቀሙም፡፡
ኢትዮጵያ በኢንተርኔት ክፍያ የመጨረሻዋ ውድ ሂሳብ ያለባት አገር ናት፡፡በዚህ ዙሪያ ፕሮፌሽኔ ነውና በቀጣይ በሰፊው መረጃ እሰጣችሁዋለሁ፡፡ላሁኑ ግን ይህ ህግ በኢትዮጵያ ከፀደቀ ስለሚከተሉት ነገሮችና ህጉ ስላስፈለገበት ዋና ምክንያት ጥቂት ልበላችሁ፡፡
ኢትዮጵያ ላይ ይህ ህግ የሚወጣበት ዋና ምክንያት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር የሚያያዝ ጉዳይ ስላለና ያንን ማወቅ በፌስ ቡክ እየተቀባበሉ መረጃ ማሰራጨትን ለመገደብ ነው፡፡የኢትዮጵያውያውያን ነገሩን ማራገብ ለጥልቁ አባላት አደጋ ስለሆነ ይህ ህግ ሊወጣ ተዘጋጅቶዋል፡፡
ፓርላማው 547 መቀመጫ ስላለውና 547ቱ ራሱ ስለሆነ ተረቀቀ ማለት ፀደቀ ማለት ነው፡፡ፀደቀ ማለት ደግሞ ያለ አንዳች ከልካይ የየትኛውም አገር ዜጋና የየትኛውም አገር መንግስት ፤መንግስታዊ የሆነና ያልሆነ ድርጅት፤የየትኛውም የሐይማኖት መሪ ነኝ ባይ ያለገደብ የኢትዮጵያን ህዝብ ለፈለገው ዓላማ ሊገለገልበት ይችላል ማለት ነው፡፡በአጭር አገላለፅ በኢትዮጵያ መንግስት ፈቃድ ብቻ ህዝቡን ከሰብዓዊ ፍጡርነት ወደ እንስሳነት ለውጦ ለገዥው አካል ማስረከብ ማለት ነው፡፡ወይም መሸጥ!ይህ ነገር ድሮ ታስቦና ተተግብሮ ቢሆን ትኩረት ላይሰጠው ይችል ነበር፡፡አሁን ግን ጫወታው ተቀይሮዋል፡፡ዓለምና ህዝቦቹዋን በአንድ በአውሬው አገዛዝ ስር የማድረግ ሂደት በተጀመረበት በዚህ ወቅት ስለሆነ የተለየ ትኩረት አስፈለገው፡፡ዓለምን በአንድ አጋዛዝ ስር ለማድረግ ደግሞ እጅግ ፈታኝ ህዝብ ያላት አገር ኢትዮጵያ ናት፡፡ኢትዮጵያውያን በዚህ ነገር በቀላሉ እንደማይጠመዘዙና መንፈሳዊ እርዳታም እንዳላቸው የተረጋገጠ ሐቅ ስለሆነ አገሪቱና ህዝቦቹዋ የተለየ ትኩረት እንዲደረግባቸው ታዞዋል፡፡ለዚህ ደግሞ በህግ ስም መታሰርና መለጎም እንዳለብን ተወስኖዋል፡፡ሌላው ዓለም አስጊ አይደለምና፡፡ስለዚህ ይህ ህግ ፀደቀ ማለት ከዓለም የተገለልንና በህግ የተገደብን በቁማችን ያለን ሙታን ሆነናል ማለት ይሆናል፡፡ይህ ህግ ፀደቀ ማለት የትኛውም አካል ቤት ለቤት እየዞረ የተዘጋጀውን ማይክሮ ችፕ በኢትዮጵያውያን እጅ ላይ ለመግጠም ይችላል፡፡በኮምፒውተር ህግ አስገዳጅነት!አለዚያ አሸባሪ ነን፡፡እስር ቤቱ ቢጠብ ሰፊ እስር ቤት ይሰራልናል እንጂ ለኛ የሚያስብ የሚቆረቆር አካል የለም፡፡ስለዚህ ይህን የአውሬውን ምልክት በሁሉም ዘንድ በሐይል ለመጫን የታሰበው ለኛ ብቻ ነው፡፡ለሌላው ኣለም በውዴታ ግዴታ እንጂ በሀይል አይደለም፡፡ ለኛ ግን አስቸጋሪ ስለምንሆን በሐይል ነው፡፡ይህንና ከዚህ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የፃፈ፣ያሰራጨ፣ሌላው ዓለም እንዴት እየተቀበለ እንዳለ የሚያሳይ ቪዲዮ የለጠፈ ኢትዮጵያን በሚመለከት ሊወጣ የተዘጋጀ መረጃ የተገኘበት፤እድሜውን በእስር ቤት ያሳልፋል፡፡እዚያም ተገብቶ ይቀርልንም፡፡
ይህ ህግ ካልፀደቀ ግን እንደ ሌላው ዓለም በፍላጎት የሚቀበል ብቻ ይቀበላል፡፡የማይቀበለውን ህግ አያስገድደውም፡፡
እንግዲህ ከላይ ስለ ማይክሮ ችፕ የተፃፈው በግምት አይደለም፡፡የምንፅፈው ዓለም ያወቀውንና በየጎግሉ ያለ፣ እነ ቢቢሲ እነ ሲኤን ኤን የዘገቡት፣መግለጫ የተሰጠበት፣ባራክ ኦባማ ራሱ እስከ 2017 ሁሉም አሜሪካዊ መግጠም አለበት ብሎ መግለጫ የሰጠበት ነገር ነው፡፡ስለዚህ የዓለም ህዝብ አውቆታል፡፡ነገር ግን የኢትዮጵያ ህዝቦች ብቻ!ልብ በሉ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ!ይህን ሂደት እንዳያውቅ በህግ ሊታደግ ነው፡፡ስለዚህ ከላይ ስለ ማይክሮ ችፕስ የፃፍኩትን ፅሁፍ በዚህ በአዲሱ ህግ በህዝብ ደህንነትና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ላይ በኮፒውተር ላይ የሚደረግ የሳይበር ጠለፋ…ወዘተ…በሚለው ህግ እስርና የገንዘብ ቅጣት ይወሰንበታል፣ይታሰራል፣ወይም ይገደላል፡፡ይህን ጉዳይ ኢትዮጵያውያን በቪዲዮና በፌስ ቡክ ካሰራጩም ሆነ ካነበቡ ወይም ፖስት ካደረጉ የስፓም መልዕክቶች ምርታቸውን ለማስተዋወቅ በሚለው አወዛጋቢ ህግ ፍርዱን ያገኛል ነው፡፡የሌላው ዓለም ህዝብ ግን መብቱ ነው፡፡እኛ ግን ስለ ጉዳዩ እንድናውቅ እንኩዋን አይፈለግም፡፡ይህ ህግ የኢትዮጵያን 99 ሚሊዮን ህዝብ አሳልፎ የመስጠት ሂደት እንጂ የሐይማኖቶችን ጉዳይ የሚመለከት ብቻ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ መንግስት አንድ ህግ ካረቀቀና ካፀደቀ ለምን ዓላማና ለምን ተግባር እነማንን ለማሰር የወጣ ህግ እንደሆነ በግልፅ እናውቃለን፡፡
ለምሳሌ የአሸባሪ ህግ ወጣ፡፡ቦምብ ያፈነዳ ሰው አይደለም የታሰረበት፡፡ከሽብር ጋር በተያያዘ በሚል ማንኛውም ግለሰብ ቤት ገብቶ የመበርበር፣ፈላጊው ራሱ አዘጋጅቶ ያመጣውን ሰነድ በተጠርጣሪው ቤት ጥሎ እጅ ከፍንጅ ተያዘ እየተባለ ለማሰር መሆኑን አይተናል፡፡ህጉ ዛሬም አለ፤ህጉ በወጣ ሰሞን ስም ዝርዝራቸው ቀድሞ የተዘጋጀ ሰዎች ታስረውበታል፡፡የታሰሩት እነማን ናቸው?አሸባሪዎች?ጥቂት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ብቻ!17 ዓመት ከቀይ ሽብር እኩል የተፈረደባቸው ጋዜጠኞች ናቸው፡፡ እስር ቤት ያሉትን ውብሸት ታዬንና እስክንድር ነጋን መጥቀስ ይቻላል፡፡ስለዚህ ይህ ህግ ሲፀድቅ የሚተገበርባቸው ሰዎች ብዕረኞችና ብሎገሮች ቪዲዮ ለጣፊዎች እንደሆኑ ማስተዋል አለብን፡፡እነዚህ ሰዎች ደግሞ በስርቆትና በሽብር ሳይሆን ህዝቡን ለማንቃት የፃፉ ናቸው፡፡ባሁኑ ሰዓት ደግሞ የግል ፕሬሶች ተዘግተው ስለቀሩና ወደፊትም ስለማይከፈቱ ብቸኛው መሰናክል ኢንተርኔት ሆኖዋል፡፡ስለዚህ እሱ ላይ መረጃዎችን ይፋ የሚያደርጉ ሊታሰሩባቸው ህግ ተረቀቀ፡፡
ይህ ደግሞ የመጨረሻው መጀመሪያ ነው፡፡ለኢትዮጵያ ህዝብ ቀናነትን መሰረት በማድረግ ብቻ ይፋ መሆን ያለበት መረጃ ይኖራል፡፡ይህ መረጃ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ቢሆን ሰው ራሱን ማዳን የሚችልበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ይህ ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ የ666ን ዓላማ ሙሉ በሙሉም ባይሆን ያጨናግፋል፡፡ይህ እንዳይሆን መንግስት ህዝቡን የማፈን ስራ ይሰራል፡፡በዚህ ምክንያት መላው ህዝብ የክፉው መንፈስ ዓላማ አስፈፃሚና ተከታይ ወታደር ማድረግ ይቻላል ማለት ይሆናል፡፡ተመልከቱ፤የትኛውም አይነት የቪዲዮ መረጃ ወይም ሌላ ተመሳሳይ ነገር ቢኖር ያንን እኔ ወይም ሌላ ሰው በቦታው ተገኝቶ ላይዘግበው ይችላል፡፡ነገር ግን የሌላው ዓለም ሰው በሆነ ቦታ ቀርፆታል ማለት ነው፡፡ያንን ይፋዊ ቪዲዮ ከሌሎች ተቀብየ ፌስ ቡክ ላይ ወይም ዩቱዩብ ላይ ብለጥፈው እኔ ወንጀለኛ እሆናለሁ ማለት ነው፡፡ለምን ለሌላው ዓለም ህዝብ ሳይከለከል ለኛ ይከለከላል?እኛ ህፃናት ስለሆንን?ወይስ የዓለም ጉዳይ ስለማመለከተን?እኮ ለምን? ብለን መጠየቃችን አይቀርም፡፡ምላሹ ግልፅ ነው፡፡ጉዳዩ ኢትዮጵያውያንን ስለሚመለከት፤ ኢትዮጵያውያን ካወቁት ቁጣ ያስነሳል ተብሎ ስለታመነ ነው መልሱ፡፡ሌላ ምን መልስ አለ?ምንም!ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ እንደሆነ መቀጠል አለበት የሚል መርህ ነው የተያዘው፡፡
ኢትዮጵያ ከኮምፒውተር ጋር በተያያዘ ምንም የሚሰለል ነገር የላትም፡፡በቤተ መንግስታችን በዋናው ዳታ ቤዝ ገለመሌ….ያ በዘመኑ ቋንቋ ማጃኮሚያ ይባላል፡፡‹‹ወታደራዊ ሚስጥራችን ተነክቶ ስላየን፣ጥቃት ስለተሰነዘረብን ወዘተ…››ውሸት ነው!
‹‹ኦሮሚያ ላይ ብጥብጥ ስላለ…››ምንናምን በጭራሽ ከዚያ ጋር አይገናኝም፡፡ህዝቡን የትኩረት አቅጣጫ ለማስለወጥና ከጀርባ ምንም የሌለ ለማስመሰል የሚደረግ ያላዋቂ ሰበብ ነው፡፡ሰበቡ ራሱ ህግ አውጭውን አካል ያጋለጠ ነው፡፡ በኦሮሚያ ክልል እነ ቲዊተር ፌስቡክ ዋትስ አፕ፣…ለአንድ ወር ዝግ ሆነው ቆይተዋል ተብሎዋል፡፡ይህ የሆነው ሰው የቪዲዮ መረጃ እንዳይቀባበልና እንዳያስፋፋ ነው፡፡ቴሌ ለዚህ ሲል ዘጋ ነው፡፡ይህ ሆነ ማለት ከብጥብጡ ጋር በተያያዘ ብዙ አሰቃቂ ቪዲዮና የምስል መረጃዎች አሉ ማለት ነው፡፡ይህን መረጃ አንዱ ላንዱ እንዳያቀብለው ነው፡፡የመቀበያ መረቦች የተዘጉት፡፡መንግስት ይህን ከፈራ አሰቃቂ ወይም የህዝቡን ቁጣ የሚቀሰቅስ ድርጊት እየፈፀመ ነው ማለት ነው፡፡ይህን ገመናውን ሳይሰራጭ ለመገደብና ለመደበቅ መሆኑ ነው፡፡ልክ በዚሁ መጠን ይህንን ህግ ከዓለም ህዝብ ለይተው እኛ ላይ ጫኑ ማለት ለኢትዮጵያ ህዝብ መድረስ የለበትም የተባለ መረጃ አለ ማለት ነው፡፡ይህ መረጃ መኖሩ ከታወቀ በሁዋላ ማጥፋት እንኩዋ ባይቻል ስርጭቱን በህግ መገደብ ብቸኛው ምርጫ ነው፡፡ቢሰራጭ እንኩዋን ለጥቂት ሰዎች ደርሶ ለውጥ ሳያመጣ ይቆማል፡፡ይህ ደግሞ ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ከማድረግ የሚከለክላቸው ደረጃ ላይ አያደርሳቸውም፡፡ዋናው የስርጭት አድማሱ አለመስፋቱ ነው፡፡በተጨማሪም ወሳኙን የቤት ስራቸውን በፅኑ መሰረት ላይ እስኪገነቡ ድረስ እንጂ ከዚያ በኋላ ህጉም ሊሻር ይችላል፡፡
ይህ ህግ ኢትዮጵያውያንን ሊጎዳ የሚችለው ግን በዋናነት በአንድ ዘርፍ ብቻ ነው፡፡
እኛ ኢትዮጵያውያን ያለ ኢንተርኔት መኖር እንችላለን፡፡ ያለ ስልክም ሰው መኖር ይችላል፡፡ኖረናልም፡፡አሁንም ለሌላው ዓለም እንጂ ለኛ ኢንተርኔት ካለ አይቆጠርም፡፡ስለዚህ የመረጃ ልውውጥ በሁሉም ዘርፍ ሊጎዳን ቢችልም ነብሳችን ግን አይነጥቀንም፡፡እኛን ሊጎዳን የሚችለው ዓለም እየተነጋገረበት ስላለው ስለ ማይክሮ ችፕ ገጠማ ግንዛቤ እንዳይኖረን በማድረግ ረገድ ብቻ ነው፡፡በአሁኑ ሰዓት ደግሞ ለኢትዮጵያውያን/ለብዙሃኑ/መንገር የሚያስፈልገውና የመረጃ ልውውጥ ወሳኝ የሚሆነው በኔ እይታ ለዚህ ጉዳይ ነው፡፡ኢትዮጵያውያን አሁን ካላቸው አቋም አንፃር ፈፅሞ ግብረሰዶማዊ መሆን እንደማይፈልጉ ነው፡፡የዓለም መሪዎች አሁን ከጀመሩትና የዓለምን ህዝብ ለበላያቸው ለክፉው መንፈስ መገልገያነት አሳልፎ ለመስጠት በሚል የያዙትን አቋምና ሂደት ኢትዮጵያውያን ላይ በቀላሉ መተግበር እንደማይችሉ ያውቃሉ፡፡‹‹አለትን በድንጋይ መፍለጥ›› ይሉታል፡፡መንግስት ካገዛቸው ግን አለቱ አፈር ይሆናል ብለው ያምናሉ፡፡በዚህ ብቻ ብዙዎችን ማዳን ሳይቻል ይቀራል፡፡ስለዚህ መፍራት ካለብን ይህን ብቻ ነው፡፡ቢያንስ እንደሌላው ዓለም ህዝብ በውዴታ ይሞክሩን እንጂ በሃል በመንግስት ተሸጠን መሆን የለበትም፡፡ይህ ፖለቲካዊ ጥያቄ አይደለም፡፡የሰብአዊ መብት ጉዳይ ነው፡፡በነፃነት ማሰብ ማገናዘብ የመቻል የመብት ጥያቄ ነው፡፡
ለምሳሌ እኔ በኮምፒውተር ጥቃት ከደረሰብኝ ከኔ የሚጠበቀው መከላከል እንጂ መከላከል ያለብኝ ራሴ ነኝ፡፡ወይም ለድረገፁ ማመልከት፡፡በአገርና በመንግስት ደረጃ ደግሞ አስቡት፡፡ጥቃት ስለደረሰብኝ ህግ አወጣለሁ ካለ፤ጥቃቱ የደረሰው ከኤርትራም ይሁን ከሌላ በህግ መገደብ እንዴት መፍትሄ ይሆናል?ለምሳሌ ኢሳያስ አፍወርቂ አስመራ ሆኖ የኮምፒውተር ባለሙያ ቀጥሮ የኢትዮጵያን ቤተ መንግስት ቢሰልልና ቢደረስበት አሁን በተረቀቀው ህግ በኢትዮጵያ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው?እንዴት?ጦር ሜዳ ያለ አማፂ የመንግስትን የመረጃ መረብ ቢጠልፍ በዚህ ህግ ፍርድ ቤት ሊቀርብ ነው?ቀድሞ ነገር አማፂ ነው የተባለውን ሰው ወይም ቡድን ለፍርድ ማቅረብ ከተቻለ መጀመሪያም በመንግስት ቁጥጥር ስር ነው ያለው ማለት አይሆንም?ስለዚህ የዚህ ህግ ዓላማ ሌላ ነው!መላውን ዜጋ በህግ ስም ለማሰር ብቻ ነው፡፡ለኢትዮጵያውያን ዜጎች፤ አገር ውስጥ ለሚኖሩ መለጎሚያ ሲባል የወጣ ህግ ነው!
እኔ ለምሳሌ የሐማኖት መምህር አይደለሁም፡፡ፖለቲከኛም አይደለሁም፡፡ምናልባት ኢአማኒ ሰው ቢኖር እንኩዋ ቃሉን ወይም ትንቢቱን ቀድሞ በተፃፈ በማንኛውም ዓለማዊ መፅሐፍ ላይ አግኝቶት ቢሆንና አሁን እየተተገበረ ካለው ነገር ጋር አገናዝቦ የዚያን ፅሁፍ እውነተኛነት ማረጋገጥ ቢችል ህን መብቱን መንግስት እንዴት ሊገድብበት ይችላል? ወደ ፊት እንዲህ ያለ ነገር ይከሰታል፤በእጃችሁ ላይ እንዲህ ያለ ነገር ይገጠማል፤ቁጥሩም 666 ነው፡፡የሚል ነገር ማንኛውም ሰው ቢያነብ አማኝ ሆነም አልሆነም በግሉ አገናዝቦ የመምረጥ መብት ይኖረዋል፡፡ መጥተው 666 እጅህ ላይ እንግጠም ሲባል እንደ ሐይማኖተኛ ሳይሆን እንደማንኛውም ማሰብ እንደሚችል ሰው ያነበብኩትን ነገር እየተተገበረብን እንደሆነ ማስተዋል እችላለሁ፡፡ስለዚህ አልፈልግም፡፡ቢል ወንጀለኛ እንዴት ይባላል?
ሁሉም ሐይማቶችና የሁሉም ቅዱሳት መፃህፍት ደግሞ ስለ ዓለም ፍፃሜና ስለ ምልክቶቹ በግልፅ ያስረዳሉ፡፡ይቺ የመማማርና መረጃ የመለዋወጫ መንገዳችን ሰው በፃፈው ህግ ከመነጠቃችን በፊት እናስተውል እላለሁ፡፡
ይህ ህግ በኢትዮጵያ ከፀደቀ በኋላ ማንም ዜጋ፣የየትኛውም ሐይማት ተከታይ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በነፃነት ስለፈጠረው አምለኩ ማውራትና መፃፍ አይችልም፡፡የሐይማኖት አባት ብለው ራሳቸው በሚሾሙዋቸው ሰዎች አማካኝነት ብቻ ነው ትምህርቱ የሚሰጠው፡፡እውነተኛ ቃሉን ሳይሆን የተጣመመ ወይም እነሱ እንድናውቅ የፈለጉትን ብቻ እየመጠኑ ማስተማር ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ይህ ህግ በኢትዮጵያ ከፀደቀ በኋላ የየትኛውም ሐይኖማት ተከታይ ይህንን ነገር መፅሐፍ ቅዱስ ያወግዘዋልና ብሎ መቃወም አይችልም፡፡ይህ ህግ በኢትዮጵያ ከፀደቀ በኋላ ስለ ሰይጣን መልካምነት እንጂ ስለ አምላክ የትንቢት ቃሎች ማንሳት አንስቶም ማውገዝ፣ህዝቡን ማስጠንቀቅ፣ወንጀል ይሆናል፡፡የሐይኖማት ግጭት ለመፍጠር በሚል ያሳስራል፡፡ህዝቡን በመከፋፈል ዓለም አቀፍ ግንኙነትን በመረበሽ፣ህዝቡን በማስደንገጥ፣በሚል ያሳስራል፡፡ይህ ህግ በኢትዮጵያ ፀደቀ ማለት ‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በአጭር ጊዜ ውስጥ 50 ሺ ቤተክርስቲያን ለማነፅ ሁለት ባለሐብቶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ለህዝቡ እየፀለዩ ነው›› የሚል ዜና ሰምተን ‹‹እነማን ናቸው?ለምን መጡ?ምን አይነት ቤተክርስቲያን ነው የሚመሰርቱት?ትምህርታቸውስ ምንድነው ኖ…!››እያልን መሞገትም ሆነ መጠየቅ፣ስለነሱ ማውራትም ሆነ ያየውን መጥፎ ነገር ይፋ አድርጎ ሌሎችን ማስጠንቀቅ ወንጀል ነው፡፡ስማቸውን በማጥፋት በሚል ያሳስራል!በቃ ዝም!
በህዝቡ ዘንድ ውዥንብር በመፍጠር፣የተዛባ መረጃ በኢንተርኔት በማሰራጨት፣ሰዎች ማንበብ የማይፈልጉትን ሽብር ፈጣሪ ፅሁፍ በስፓም ሜሴጅ በመላክ በሚል ከአገር ባለቤትነት ብቻ ሳይሆን በማንነታችን ማዘዝ አለመቻላችንን እስቅናውቅ ድረስ አቁም!ግባ!ታሰር!ይለናል የኮምፒውተር ህግ!ይህ ነው ቀጣዩ ነገር፡፡
አሁንም ልብ በሉ!ለምሳሌ እነዚህ ሁለት ነጮች መጡ፡፡ለባለ ስልጣናት ፀለዩ፡፡ይሁን እሽ፡፡የሐይማኖት ነፃነት በህገ መንግስቱ ስላለ ማንም ሰው የመሰለውን ሐይማኖት መከተልና ማምለክ ይችላል፡፡ነገር ግን ሰዎቹ የመጡት ከባዕድ አገር ነው፡፡አጀማመራቸውም ግራ አጋቢ ነው፡፡ስለዚህ እኔ እንደ ዜጋ ስለ ሰዎቹ ማንነት ማለት ያለብኝን ወይም መጠየቅ ያለብኝን ነገር ወንድሜን ቤተሰቤን ልጠይቅ እችላለሁ፡፡ነገ በግድ ተቀበል ቢሉኝ እንቢ እላለሁ፡፡መብቴ ስለሆነ፡፡እንቢ የማለት መብቴን ግን በአዲሱ ህግ መንግስት ቀምቶኛል፡፡ህጉ ይሄ ነው፡፡ስለዚህ ይህ ፀደቀ ማለት አሁንም ሆነ ነገ ለማክሮ ችፕ ገጠማ እጃችንን እንደሰጠን ቁጠሩት፡፡
50 ሺ ቸርች!ቆይ እነማን ናቸው?ዓላማቸውስ ምንድን ነው?ከየት መጡ? ምን አይነት ቤተክርስቲያን ነው የሚያቁዋቁሙት?ከሁሉም በላይ ለምን ኢትዮጵያን መረጡ?አምላክን የማያውቁ ዜጎች ያሉዋት አገር ኢትዮጵያ ስለሆነች?ዕውቀት ስለሌለን?አስተምሩን ብለን ጠርተናቸው?በእምነት ላይ እምነት ሊጨምሩልን?ያለንን እምነት ሊንዱብን?ስላልተጠመቅን ሊያጠምቁን?ወንጌል ስላልተሰበከልን ሊሰብኩልን?ይህን ጥያቄ ነው መንግስት በፌስ ቡክና በሌሎች የመረጃ መለዋወጫ መንገዶች እንዳይጠየቁ የፈለገው፡፡እነዚህ ሰዎች የመጡት በይፋ ነው፡፡ለዓለም አቀፍ ሚዲያ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚሄዱ፣ሄደውም 50 ሺ ቸርች እንደሚከፍቱ በይፋ ተናግረዋል፡፡ይህን ዓለም ያውቃል!ታዲያ እኛ የሐገሪቱ ባለቤቶች ይህን የማወቅ መብት ለምን እንነፈጋለን?ሚስጥሩ ሌላ ካልሆነ ለምን ህግ ያወጡብናል?ስለ ሐይማኖት ባናበሳ ስለ መሬት ቅርምት ማንሳት አንችልም?
ለማየት ያብቃችሁ፤ይህ ህግ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ከሆነ ከዚህም ያለፈ ጉድ እያየን ዝም እንላለን፡፡ወይም ሞትን መምረጥ ወይ ዝምታን መምረጥ!
ልብ በሉ!እነዚህ ሰዎች 50 ሺ ቸርች ሊሰሩ መምጣታቸውን የሰማነው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አይደለም፡፡ማንም አልነገረንም፡፡ዝቅ ብላችሁ ሊንኩን ተጭናችሁ ሙሉ የእንግሊዝኛ ዘገባውን ማየት ትችላላችሁ፡፡መረጃው ለዓለም ህዝብ ይፋ የሆነ ነው፡፡
ስለዚህ በቀላሉ አገኘነው፡፡እነሱም በድብቅ አልመጡም፡፡የሚደብቀው መንግስት ነው፡፡እነሱ ያልደበቁንን የገዛ መንግስታችን ይደብቀናል፡፡
ይህን ህግ የማውጣት ጉዳይ ቀና ሃሳብ ቢይዝ ኖሮ በቴሌቪዥን የማይረቡ ስብሰባዎችን እንደሚያሳዩን ሁሉ ስለዚህ ህግም በቂ የሆነ ትንተና መስጠት ይችሉ ነበር፡፡ግን ደባ ነው!
ተፃፈ ተረቀቀ ፀደቀ በነጋሪት ጋዜጣ ታወጀ አበቃ፡፡ሆነ ብሎ ነጋሪት ጋዜጣ የሚከታተል ዜጋ ምን ያህል ነው?ስለ ህጉ የምናውቀው ልንያዝ ስንልና ከተያዝን በኋላ ነው፡፡
ይህ ህግ በኢትዮጵያ ሊፀድቅ እንደሆነ በጋዜጣ ወይም በኢንተርኔት ሰማን፡፡ያውም ተሸራርፎና ተዘገበ ለማለት ያህል እንጂ ሙሉ ዝርዝሩ አልተነገረም፡፡ግን ዘዴውን ስለለመድነው አንዱን አንቀፅ ከነገሩን በቂ ነው፡፡ይህ ህግ በኢትዮጵያ ከፀደቀ ሌላ ብዙ 50 ሺ ቸርቾች፣ሌላ ብዙ 50ሺ ነገሮች ይተክሉልናል፡፡
ይህ ህግ ከፀደቀ የሁሉም ሐይማኖት ተከታይና ሐይማኖት የሌለው ዜጋ ሁሉ! ሁሉም ኢትዮጵያዊ ማን ለምን እንደመጣ አለማወቅ ብቻ ሳይሆን ማን መቸ መጥቶ ምን እንደሚያደርግ፣የሚደረገው ነገር ለምን እንደሆነና ውጤቱ ምን እንደሚመስል የማወቅ እድል አይኖርም፡፡በምን ሰዓትና የት ቦታ በኢትዮጵያውያን ላይ ማይክሮችፕ እንደሚገጠም ማወቅ ቀርቶ መጠርጠር አይቻልም፡፡ይህ ሆነ ማለት ደግሞ ወደድንም ጠላንም የሰይጣን ወታደር ሆነህ በወንድምህ ላይ ትነሳለህ!ሳታውቀው ሳገባህ ወላጆችህን ታሳድዳለህ፡፡ራስህን መቆጣጠር እስካትችል ድረስ አገልጋይ ትሆናለህ፡፡ይህን አይነቱን ነገር ልወቅ ብትል ብቻህን ታውቅና ዓላማው ሳይገባህ ሌሎችን ማዳንና ማስጠንቀቅ ሳትችል ህብረትም ሳትፈጥር እያወከውም ቢሆን ትጠፋለህ!ይህን አይነቱን ቃላት አይደል ህዝቡን ማስፈራራት ብሎ የሰየሙትና ያረቀቁት?ማን ማንን ያስፈራራል?አፍንጫችን ስር ምን እንየሆነ እንዳለ እያየን ካልፈራን እንዴት በወሬና በመረጃ ልውውጥ እንፈራለን?!ፍርሀታችንን ከህጉ ጋር አብረን ካልገደልነው አስከፊ ነገር ነው የሚጠብቀን፡፡ከጥሩ አሟሟትና የሠይጣን ወታደር ሆኖ ከሚሞተው ክፉ ሞት የቱ ይሻላል ይሆን?
ይህ ህግ በኢትዮጵያ ፀደቀ ማለት ሁሉም ነገር በነሱ ቁጥጥር ስር እንደሆነ እርግጠኛ ሁኑ!ከዚህ ህግ መፅደቅ በኋላ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንኳን በሐይማኖቱ፣እንኳን በአገሩ፤ በገዛ ማንነቱ ማዘዝ አይችልም!እናስተውል!አስተውለንም በአንድ ድምፅ ህጉ እንዳይፀድቅ የተቻለንን እንጣር እላለሁ፡፡ ይህን ፅሁፍ ከፋም ለማም ሁሉም ሰው ማንበብ አለበት ብላችሁ የምታምኑ ሁሉ ሼር አድርጉት፡፡Read more..
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
አረተዉ ኢትዮጵያዊያን እኔ ለማመን ከበደኝ????????
ReplyDelete